




ብዙ ህይወት የቀጠፈው ወንዝ ድልድይ ተሰርቶ ተመረቀ
ደባርቅ፡- ሐምሌ 16/2018(ሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን)
በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ስር በደበር ቀበሌ የሚገኘው ሙገጭት ወንዝ ድልድይ ከ23 መሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ ተግንብቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የዞኑ ገጠር መንገድ ትርንስፖረትና ሎጅስቲክስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በመርቃቱ ስነስርአት የእንኳን ድስ ያላችሁ መልእክት ያስተላለፉት የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲቫ አቶ ጌትነት ፀጋየ ከደባርቅ ጃናሞራና በየዳ መንገድ ሳይሰራ በፊት የእግር መንገድ ሆኖ ያገለግል ስለነበር ወንዙ ሲሞላ የመንገደኞችን ህይወት ሲቀጥፍ እንደነበርና መንገደኞችን ያስተጓጉል እንደነብር ተናግረዋል፡፡
ከንቲባው አያይዘውም ከዚህ በኋላ ድልድዩ እንዳይጎዳ የአካባቢው ማህበረሰብ በባለቤትነት ሊጠብቀው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ስለግንባታው ገላፃ ያደረጉት የሰሜን ጎንደር ዞን ገጠር መንገድ ትርንስፖረትና ሎጅስቲክስ መምሪያ ኃላፊ አቶ እሸቴ መልኬ የክልሉ ገጠር መንገድ ትርንስፖረትና ሎጅስቲክስ ቢሮ በመደበው 23 ነጥብ ስምንት ሚሊየን ብር 22 ሜትር ርዝመትና ሰባት ሜትር ከፍታ እንዲኖረው ተደረጎ መገንባቱን አስረድተዋል፡፡
አቶ እሸቴ አያይዘውም በአባይ ግድብ የገጠር መንገዶች ባለሙያዎች ህብረት ስራ ማህበር መገንባቱን ገልፀው ግንባታው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ የቀበሌውን ህዝብ አመስግነዋል፡፡
ይህ ወንዝ ሰዎች ከቤታቸው እንደወጡ ሳይመለሱ በማስቀረት የብዙ ሰዎችን ህይወት እንደቀጠፈ የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ድልድዩ ተመርቆ አገልግሎት በመስተጡ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡
ለግንባታው መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም በሰሜን ጎንደር ምክትል አስተዳዳሪና ትምህርት መምሪያ ኃላፊ በአቶ ክቡር አሰፋ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
በድልድይ ምርቃቱ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣የደባርቅ ከተማና ወረዳ አመራሮችና የቀበሌው ህዝብ ተሳትፏል፡፡